አይቴል ሞባይል 10ኛ አመቷን እሁድ ጥቅምት 05 በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በደማቅ ስነ ስረዓት ታከብራለች

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

Continue reading “አይቴል ሞባይል 10ኛ አመቷን እሁድ ጥቅምት 05 በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በደማቅ ስነ ስረዓት ታከብራለች”

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ – ቼልሲ Vs አርሰናል

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


በመጀመሪያው የSuper Sunday ሳምት ጨዋታዎች ላይ ቼልሲዎች አርሰናልን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ። ቢያሸንፉ በአርሰን ዌንገር ላይ ይበልጥ ጫና እንደሚያሳድሩባቸውም እርግጠኞች ናቸው።


አርሰናሎች – ከባለፈው አመት ቶፕ-6 የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ጋር ባደረጓቸው 13 የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ላይ ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም። እንዲሁም ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ተጉዘው ካደረጓቸእ ይለፉት 8ት ጨዋታዎች በ7ቱ ተሸንፈዋል።

▪ ዌንገር ከትላልቆቹ ክለቦች መሃከል ያለመጨረሻ ግዜ ያጣጣሙት ድል ከ1000 ቀናት በፊት ሲሆን ያኔም ማንቸስተር ሲቲን 2-0 በሆነ ውጤት ያሸነፉበት የ 2015ቱ ጨዋታ ነው።

▪ ምንም እንኳን በሜይ ወር ላይ የFA Cupን ዋንጫ ቢበሉም በፕሪሚየር ሊጉ የሊቨርፑል እና ስቶክ ሲቶ ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ በመሸነፋቸው ዌንገር አሁንም ጫና ውስጥ ይገኛሉ።

▪ ለመጨረሻ ግዜ በሊጉ ያደረጓቸውን የመጀመሪያ ሦስት ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎች የተሸነፉት በ 1954 ላይ ነው።


ቼልሲዎች – የአምናው የሊጉ ሻምፒየኖች በመጀመሪያው የሊጉ መክፈቻ ጨዋታ ላይ በበርንሌይ ከተሸነፉ በኃላ ቀስ በቀስ ወደ ብቃታቸው ተመልሰዋል።

▪ ቶተንሃም ፣ ኤቨርተን እና ሌስተር ሲቲን ካሸነፉ በኃላ የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን አርሰናልን የሚገጥመው በሙሉ ራስ መተማመን ነው።


የቡድን ዜናዎች – የቼልሲው አማካይ ዳኒ ድሪንክ ወተር እስከ የፊታችን ኦክተበር ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች እረፍት ድረስ ወደ ሜዳ አይመለስም።
ለአራት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅም ይጠበቃል።

ቼልሲዎች ለQarabag contest እንዳደረጉት ሁሉ ቡድናቸውን በመቀያየርና ሮቴት በማድረግ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ኢዲን ሃዛርድ ለመጀመሪያ ግዜ በዚህ ሲዝን ቋሚ ሆኖ ለመሰለፍ የሚፎካከር ይሆናል።

▪ አርሰናሎች በርካታ የዋናው ቡድን ተሰላፊዎቻቸውን እንደሚጠሩ ይጠበቃል።

▪ ዌንገር በEuropa League ድላቸው ላይ ዘጠኝ የቡን ተጭዋቾችን ቅያሬ አድርገው ነበር። ሆኖም እንደነ ፒተር ቼክ፣ ሜሱት ኦዚል፣ ሎረንት ኮሽሌይኒ እና አሌክሳንደር ላካዜቲን የመሳሰሉት ኮከቦቻቸውን ለስታምፎርድ ብሪጁ ወሳኝ የሊጉ ፍልሚያ ላይ ወደ ዋናው ቡድን ቋሚ ተሰላፊነት ይመልሷቸዋል።

▪ አሌክሲስ ሳንቼዝ በበኩሉ በሃሙስ ምሽቱ ዩሮፓ ሊጉ ጨዋታ ላይ ሙሉ ዘጠና ደቂቃዎችን ከተጫወተ በኃላ ለእሁዱ ፍልሚያም ዝግጁ ነው። ቲዎ ዋልኮት በበኩሉ የ(calf) ህመም አለበት። ፍራንቺስ ኮክለን (hamstring) እና ሳንቲ ካዞርላ ደግሞ (ankle) ጉዳቶች ስላሉባቸው ከጨዋታው ውጪ ናቸው።


Opta stats የኦፕታ ስታቶች

▪ ቼልሲዎች ባለፈው ካደረጔቸው አምስት የፕሪሚየር ሊጉ የሜዳቸው አርሰናል ጨዋታዎች ላይ በኦክቶበር ወር ላይ 2011; 3-5 በሆነ ውጤት ከመሸነፋቸው በቀር ሁሉንም አሸንፈዋል።

▪ መድፈኞቹ በባለፉት 12 የሊጉ የስታምፎርድ ብሪጅ ጨዋታዎቻቸው ላይ ጎል ሳይቆጠርባቸው ወጥተው አያውቁም። በስምንቱ እያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ሁለት-ሁለት ጎሎች መረባቸው ላይ አርፎአል።

▪ አርሰናሎች ከቼልሲ ጋር ያደረጔቸውን ያለፍ0ት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አስተናግደዋል። ይሄ ሪከርድ በአንድ ነጠላ ተቀናቃኛቸው ላይ ከሜዳቸው ውጪ ከደረሰባቸው አምስት ሽንፈቶች ጋር እኩል ነው። (ከ2009-2013 ባሉት አመታት ውስጥ በማንቸስተር ዩናይትድ ለተከታታይ አምስት ጊዜያት ያህል ተሸንፈዋል).

▪ አርሰናሎች በነገው ጨዋታ ላይ ጎል የሚቆጠርባቸው ከሆነ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ በረጅም ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጎል በማስተናገድ ታሪክ ይጋራሉ። (ከ 1999 እስከ 2012 ባሉት ሲዝኖች ላይ በ13 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ቢያንስ አንድ ጎሎችን አስተናግደው ወጥተው ነበር).

▪ ቼልሲዎች ባለፉት ባደረጎቸው 23 ተከታታይ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎቻቸው ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ጎሎችን ሳያስቆጥሩ አልወጡም። ከነዚህ ጨዋታዎች መሃል በግማሽ ያህሉ (12) ሦስት እና ከዛ በላይ ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል።

▪ አርሰናሎች የመጀመሪያዎቹን ሁለት የፕሪሚየር ሊጉ ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል። (0-4 vs በሊቨርፑል እና 0-1 vs በስቶክ ሲቲ) – ለመጨረሻ ግዜ በሊጉ ከሜዳቸው ውጪ በሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተሸነፉት በ1954-55 ላይ ነበር።

▪ አርስናሎች በፕሪሚየር ሊጉ ከቶፕ-6 ክለቦች ጋር ባደረጎቸው የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎች ላይ ለመጨረሻ ግዜ ማሸነፍ የቻሉት በጃንዋሪ ወር ላይ ሲሆን በ 2015 (2-0 ማንቸስተር ሲቲን ሲያሸንፉ ነው)። ከዛ በኃላ ከቶፕ-6 ክለቦች ጋር ያደረጔቸው ያለፉት 13 ጨዋታዎች በስምንቱ ሲሸነፉ በአምስቱ አቻ ወጥተዋል።


Paul Merson’s prediction የፖል ሜርሰን ግምት

የጨዋታው ውጤት የሚወሰነው ማን ቀድሞ የመጀመሪያውን ጎል ያገባል በሚለው ነው። አርሰናሎች ቀድመው የሚያገቡ ከሆነ ጨዋታውን እያያቹ ‘wow, they look decent’ ልትሉ ትችላላቹ። በራስ መተማመናቸው ይመጣል ሲያሸንፉ ደግሞ ጥሩ የሚሆኑ ድንቅ ተጭዋቾችን ይዘዋል።

ሆኖም ሲሸነፉ ግን አብዛኛዎቹ ተጭዋቾቻቸው ይጠፋሉ ሜዳ ውስጥም ያሉ አይመስሉም። ቅርፃቸው ይጠፋል ቡድኑ ይርመሰመሳል። የመጀመሪያውን ጎል በቼልሲ ካስተናገዱ ነገሮች ሁሉ ከባድ ይሆንባቸዋል። ሰዎች የበርንማውዝን ጨዋታ ከተመለከቱ በኃላ ‘ፓፓ ምን አይነት ድንቅ ጨዋታ ነበር’ እያሉ ይነግሩኝ ነበር። ሆኖም የትኛውንም የቡድን አባል መርጣቹ ብታጫውቱ ጨዋታው ከበንማውዝ ጋር ነው።

አርሰናሎች ቀድመው ጎል የሚያስቆጥሩ ከሆነ ጨዋታው ለመመልከት አጉአጊ ይሆናል። ሆኖም የሚያስቆጥሩ ግን አይመስለኝም።

▪ PAUL PREDICTS: 3-0 (14/1 with Sky Bet )


Betting ቁመራ

▪ ቼልሲዎች በSky Bet’s 4/5 አርሰናልን የማሸነፍ የተሻለ እድል ተሰጥቶአቸዋል

▪ አርሰናሎች በበኩላቸው 3/1 ዋጋ ተተምኖላቸዋል

▪ አቻ በ 29/10 ላይ ተቀምጧል


በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

አርብ ከሰአት በኃላ ላይ የወጡ በርካታ ተጭዋቾችንና ክለቦችን የተመለከቱ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎች አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ ወሬዎች

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


REAL PLOT DE GEA & HAZARD RAID

ሪያል ማድሪዶች በማንቸስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደ ሂያ እና በቼልሲው የጨዋታ አቀናባሪ ኢድን ሃዛርድ ላይ በድጋሚ ፍላጎት አሳድረዋል ሲል የስፔኑ Don Balon ጋዜጣ ዘገበ።

የላ ሊጋው ግዙፍ ክለብ ከጥቂት አመታት ጊዜ ጀምሮ ተጭዋቾቹን ወደ ሳንቲያጎ በርናባው ለማዛወር ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን አሁን ለረጅም ጊዜያት ያህል ሲጥሩ የቆዩባቸውን ዝውውሮች በ2018 ላይ ለማጠናቀቅ ከወዲሁ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።


WENGER WANTS CUADRADO

አርሰን ዌንገር የቀድሞ የቼልሲን የፊት ተሰላፊ ጁአን ኩአድራዶ ከጁቬንቱስ በማዛወር ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመመለስ ጥረት ያደርጋሉ። አሌክሲስ ሳንቼዝ የሚለቅ ከሆነም ምትኩ ሊያደርጉት አስበዋል ብሏል TMW .

መድፈኞቹ ከወዲሁ ክለቡን የሚያጠናክሩላቸው ተጭዋቾችን እያሰሱ ሲሆን ሜሱት ኦዚልን ጨምሮ በፍላይ ኢምሬትስ በክለቡ የመጨረሻ የኮንትራት አመታቸው ላይ ይገኛሉ።


ALEXIS ON REAL RADAR

ከአርሰናል ክለብ መልቀቅ የሚፈልገው አሌክሲስ ሳንቼዝ በ2018 ሪያል ማድሪዶች ሊያዛውሯቸው በዝርዝር ከያዟቸው አራት የፊት መስመር ተሰላፊዎች ውስጥ አሌክሲስ ሳንቼዝ አንዱ ነው ብሏል Don Balon .

ቺሊያዊው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ለመዛወር ተቃርቦ ዝውውሩ የከሸፈበት ሲሆን የኮንትራቱ የመጨረሻ አመት ላይ ይገኛል። የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ፒር ኢምሬክ ኦበምያንግ ፣ የባየር ሙኒኩ ሮበርት ሎዋንዶውስኪ እና የቶሪኖው አንድሪያ ቤሎቲ ሌሎቹ በሪያል ማድሪድ የዝውውር ራዳር ውስጥ የገቡ ተጭዋቾች ናቸው።


INTER TO INCREASE ICARDI CLAUSE

ኢንተር ሚላኖች የአጥቂያቸው ማውሮ ኢካርዲን ኮንትራት ውል ማግረሻ ሂሳብ በእጥፍ በመጨመር ወደ £190 million ሊያሳድጉት አቅደዋል። በዚህም ሳቢያ ፈላጊ ክለቦቹን ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለማሸሽ ይፈልጋሉ ብሏል Premium Sport .

አርጀንቲናዊው በሳንሲሮ የሚያቆየውን አዲስ ውል የፈረመው ገና በOctober ወር 2016, ላይ ሲሆን አዲስ ኮንትራት ድርድር ማድረግ ደግሞ ከወዲሁ ጀምሯል።


MADRID JOIN RACE FOR BARCA TARGET

ሪያል ማድሪዶች የባርሴሎናውን የዝውውር ኢላማ ማክሲሜ ሎፔዝን ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ተቀላቅለዋል ብሏል Sport ጋዜጣ።

ሎስ ብላንኮዎቹ በቅርቡ በ19 አመቱ የማርሴይ ታዳጊ ባለተሰጥዎ ላይ የክላሲኮ ተፎካካሪዎቻቸው ፍላጎት ማሳደራቸው የታወቀ ሲሆን በያዙት አዲስ ታዳጊዎችን የማዛወር ፖሊሲ ሳቢያ ሊያስፈርሙት ይችላሉ።

የዚነዲን ዚዳን በማድሪድ አሰልጣኝነት መኖር ሪያል ማድሪዶች ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ልጁን ቀድመው ሊያዛውሩ የሚችሉበትን የተሻለ እድል የሚሰጧቸው ሲሆን ለማርሴይ ዋናው ቡድን 43 ጨዋታዎችን መጫወት ችሏል።


ፖል ፖግባ ለአራት ሳምንታት ያህል በጉዳት ከሜዳ መራቁ ይታወሳል። ተጭዋቹ የሚያመልጡት 6ት ጨዋታዎች የኤቨርተን፣ ሳውዛምፕተን፣ ክሪስታል ፓላስ፣ በርተን አልቢዮን፣ ሲ.ኤስ.ኬ ሞስኮ እና ሊቨርፑል ናቸው። [bbc]

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ሃሙስ ከሰአት በኃላ የወጡ ሰፊ ዜናዎች – Thursday Papers Talk

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


NO OZIL TALKS SINCE FEBRUARY

አርሰናሎች እና ሜሱት ኦዚል ከፌበርዋሪ ወር ጀምሮ በአዲሱ ኮንትራቱ ዙሪያ ምንም አይነት ንግግር እንዳላደረጉ የጀርመኑ Sport Bild ጋዜጣ ዘገበ።

ኦዚህ በአመቱ መጨረሻ ላይ ከኮንትራቱ ሙሉ ለሙሉ ነፃ የሚሆን ሲሆን ከዚህ በፊት አመታዊ €9 million ሂሳብ በሚያስገኝለት አዲስ ኮንትራት ዙሪያ ከክለቡ ጋር ድርድር ማድረግ ጀምሮ ነበር።

ሆኖም ከዛ በኃላ ድርድሩ በአርሰን ዌንገር በክለቡ መቆየት አለመቆየት ጥርጣሬ ሳቢያ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ይታወሳል።


LIVERPOOL LOOK AT DE VRIJ

ሊቨርፑሎች የላዚዮውን ተከላካይ ስቴፋን ዲ ቨርጂ በክረምቱ ለማዛወር ሙከራ ያደርጋሉ። ከርሱ በተጨማሪም የሳውዛምፕተኑ ተለላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክን ለማዛወር በድጋሚ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ሲል የጣሊያኑ እትም Calciomercato, በ Daily Mirror ጋዜጣ በኩል ዘግቧል።

ዲ ቨርጂ በአመቱ መጨረሻ ላይ ከኮንትራት ነፃ የሚሆን ሲሆን አእስካሁን ድረስ ምንም አይነት አዲስ ስምምነት መፈራረም አልቻለም። ቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ላዚዮ እና ጁቬንቱስ የተጭዋቹ ፈላጊ ክለቦች መሆናቸው ተነግሮአል።


ATLETICO CLOSE ON COSTA

አትሌቲኮ ማድሪዶች የቀድሞ አጥቂያቸውን ዲያጎ ኮስታ በድጋሚ ለማዛወር ከጫፍ ደርሰዋል ብሏል የስፔኑ ጋዜጣ Marca .

ሪፖርቱ እንደዘገበው ከሆነ ሁለቱም ክለቦች ኮስታ ከብራዚል ወደ አውሮፓ ለመመለስ ፍቃደኛ መሆኑን ከገለፀ በኃላ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ድርድር ማድረግ ጀምረዋል።


ARSENAL STILL ON JANKTO TRAIL

አርሰናሎች አሁንም የዩዲኒዜውን አማካይ ጃኩብ ጃክቶን እድገት በቅርበት ሆነው እየተከታተሉት ይገኛል ብሏል የCalciomercato ዘገባ።

ኤሲ ሚላን እና ጁቬንቱስ በጃክቶ ዝውውር ላይ ፍላጎት ያሳዩ ሌሎች ክለቦች ሲሆኑ ተጭዋቹ ከዚህ በፊት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተዛውሮ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው መግለፁ ይታወሳል።


BARCA TO BID AGAIN FOR SERI

ባርሴሎናዎች የኒንሱን አማካይ ጂያን ሚቼል ሴሪን በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ለማዛወር አዲስ ጥረት ለማድረግ ዝግጁ ናቸው ብሏል Sport ጋዜጣ።

ሴሪ ባርሴሎናዎች ጨርሰነዋል ብለው ባሰቡት የፊሊፕ ኩቲንዎ እና አንጀል ዲ ማሪያ ዝውውር ሳቢያ ተቃርቦ የነበረው የሴሪ €40 million ካታሎን ዝውውሩ ከተጨናገፈበት በኃላ የተበሳጨ ቢሆንም የካታላኑ ክለብ ግን በድጋሚ አይቬሪኮስታዊውን አማካይ ለማዛወር በድጋሚ ጥረት ያደርጋሉ።


MADRID PLAN ATTACKING OVERHAUL

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በሳንቲያጎ በርናባው ቡድን ውስጥ ያላቸውን የአጥቂ መስመር ተሰላፊ ተጭዋቾችን ለማደስ ዝግጁ ናቸው ብሏል Don Balon .

ፔሬዝ ካሪም ቤንዜማን ለመሸጥ ፍቃደኛ የሆኑ ሲሆን እንዲሁም ጋሬዝ ቤልንም በመሸጥ ለዝውውር የሚሆናቸውን በርካታ ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳቦችን ለመሰብሰብ ተሰናድተዋል። ተጭዋቾቹን ለማዛወርም አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትዶች እንደ ቅደም ተከተላቸው ዝግጁ ሆነዋል።

እናም ብላንኮዎቹ ገንዘቡን የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ አንቶኔ ጋሬዝማን እና የጁቬንቱሱን አጥቂ ፓብሎ ዳይባላን ለማዛወር ይጠቀሙበታል ተብሏል። ሁለቱን አጥቂዎች በማዛወር ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ሊያጫውቷቸውም ይፈልጋሉ።


MAN UTD READY £100M GRIEZMANN BID

ማንቸስተር ዩናይትዶች የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ አንቶኔ ጋሬዝማን ለማዛወር የ£100 million ሂሳብ በቀጣዩ አመት ላይ ለማቅረብ ተሰናድተዋል ብሏል Daily Star .

ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል በክረምቱ አዲስ ኮንትራት ከመፈራረሙ በፊት ወደ ኦልትራፎርዱ ክለብ ይዛወራል በሚል ስሙ በስፋት ተያይዞ ሲወራ የቆየ ቢሆንም አትሌቲኮዎች በፊፋ የዝውውር እገዳ ከተጣለባቸው በኃላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመዛወር ህልሙ ሁሉም ነገር ተቋጭቷል።

ሆኖም ጆዜ ሞሪንዎ ጋሬዝማን ማንቸስተር ዩናይትድን በ2018ቱ የዝውውር መስኮት ላይ እንዲቀላቀል እንደሚያደርጉት ተስፋ አድርገዋል። በዛም ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አጋሮቹ ፖል ፖግባ እና አንቶኔ ማርሻል ጋር ፊት መስመር ላይ እንደሚያጣምሩት ይጠበቃል።


በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

This Week Fixtures – የ5ቱም አውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የቅዳሜ የእሁድ እንዲሁም የሰኞ መርሀ ግብሮች (በኢትዮጵያ ቀንና ሰአት አቆጣጠር)

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

Continue reading “This Week Fixtures – የ5ቱም አውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የቅዳሜ የእሁድ እንዲሁም የሰኞ መርሀ ግብሮች (በኢትዮጵያ ቀንና ሰአት አቆጣጠር)”

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ማንቸስተር ሲቲ Vs ሊቨርፑል

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ቶፕ-4 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ካደረጉአቸው ሦስት የሊጉ ጨዋታዎች 7ት ነጥቦችን ሰብስበዋል። ሆኖም ማን ሲቲዎች እስካሁን ድረስ በኢትሃድ ሦስት ነጥብ ያላገኙ ሲሆን ከኤቨርተን ጋር አቻ 1-1 ተለያይተዋል።

በተቃራኒው ሊቨርፑሎች በሜዳቸው ያደረጉትን ሁለቱንም ጨዋታዎች ያሸነፉ ሲሆን አርሰናልን 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት የረቱበት አይረሳም። ብቸኛ ነጥብ የጣሉበት ከሜዳ ውጪ ጨዋታቸው ከዋትፎርድ ጋር 3-3 የተለያዩበት ነው።

የቡድን ዜናዎች Team news

በማን.ሲቲ በኩል በጉዳት ጨዋታው ሊያመልጠው የሚችለው ብቸኛው ተጭዋች ኢካይ ጉንዶጋን ሲሆን አማካዩ ባለፈው አመት ከደረሰበት ከባድ የጉልበት ጉዳት ቢያገግምም አሁንም ሙሉ ለሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ አልሆነም።

ካይል ወልከር በበኩሉ አንድ ጨዋታ ከተቀጣ በኃላ ተመልሷል።

የሊቨርፑሉ የጨዋታ አቀጣጣይ ፊሊፕ ኩቲንዎ በዚህ ሲዝን እስካሁን አንድም ጨዋታ አላደረገም። ብራዚላዊው ከብሄራዊ ቡድኑ ጋራ የተጫወተ ሲሆን የባርሴሎና ዝውውር ከተጨናገፈ በኃላ ወደ አንፊልድ ይመለሳል። ሆኖም የርገን ክሎፕ በባለፉት ሦስት ሳምንታት የተጠቀሙባቸውን ተጭዋቾች እሚቀይሩ አይመስሉም አሁን አሌክስ ኦክስሌይድ ቸምበርሌይንም ለአማራጭነት ቀርቦላቸዋል።

አደም ላላና (thigh) እና ናትናኤል ክሌይን (hamstring) ጨዋታው እንደሚያመልጣቸው ይጠበቃል።

ከአርሰንል ጋር በተደረገው ጨዋታ ክሎፕ ሲሞን ሚኞሌትን በሎሪስ ካሪየስ አስቀምጠውት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የሚያሰልፉት ይመስላል።

ግምታዊ አሰላለፎች Starting line-ups

የማንቸስተር ሲቲ XI: Ederson, Walker,
Kompany, Otamendi, Mendy, De Bruyne,
Fernandinho, Silva, Bernardo Silva, Jesus,
Sterling

የሊቨርፑል XI: Mignolet, Oxlade-
Chamberlain, Matip, Lovren, Moreno, Can,
Henderson, Wijnaldum, Salah, Firmino, Mane

የአቋማሪ ድርጅቶች Bettings odds (via 888Sport)

ማንቸስተር ሲቲ ያሸንፋል: 17/20
አቻ: 14/5
ሊቨርፑል ያሸንፋል: 16/5

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ሰኞ ከሰአት በኃላ ላይ የወጡ በርካታ ተጭዋቾችንና ክለቦችን የተመለከቱ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎች አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ ወሬዎች

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


የ30, አመቱ የባርሴሎና ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የ25 አመቱ ብራዚላዊ ኔይማር ክለቡን ከለቀቀ በኃላ እና ክለቡ በምትኩ ሌላኛውን የ25 አመቱን ብራዚላዊ አማካይ ፊሊፕ ኩቲንዎ እና የ29 አመቱን አርጀንቲናዊ አንጀል ዲ ማሪያ ማዛወር ባለመቻሉ ሳቢያ እርሱም በክለቡ ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ እያሰበበት ይገኛል። (Diario Gol, via Daily Express)

 

አርሰን ዌንገር በክረምቱ የሁለት አመት አዲስ ኮንትራት ከመፈራረማቸው በፊት ክለቡን ስለመልቀቅ አስበው እንደነበር አምነዋል። ሆኖም ፈረንሳዊው አለቃ መድፈኞቹ አሁንም በዚህ ሲዝን የሊጉን ዋንጫ ሊያነሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። (Daily Mirror)

 

ማንቸስተር ዩናይትዶች በ26, አመቱ የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ አንቶኔ ጋሬዝማን ዝውውር ላይ በድጋሚ ፍላጎታቸው አገርሽቷል። ምክኛቱ ደግሞ ቀድሞ የነበረው የ£184m ውል ማፍረሻው አሁን በግማሽ ቀንሶ ወደ (€100m) በመውረዱ ነው። የስፔኑ ክለብ የዝውውር እገዳ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የሚነሳ ይሆናል። (Mundo Deportivo, via Daily Express)

 

የ28 አመቱ የቶተንሃም ቤልጂየማዊ ኢንተርናሽናል ተከላካይ ቶቢ አልደርዋየርድ በክለቡ ያለው ቀሪ ኮንትራት እስከ 2020 ድረስ የሚያልቅ ሲሆን በበርካታ ታላላቅ ክለቦች መፈለጉን በመግለፅ ክለቡ አዲስ የተሻሻለ ኮንትራት እንዲያቀርብለት ጠይቋል። (The Sun)

 

የአርሰናሉ አሌክሲስ ሳንቼዝ ባለቀ ሰአት ስለተጨናገፈበት የማን.ሲቲ ዝውውር ተንፍሷል። የ28 አመቱ አጥቂ በኢንስታግራም አካውንቱ ልልይ እንደፃፈው ከሆነ: “You will realise that what today seems like a sacrifice, will end up being the greatest achievement of your life.” (Manchester Evening News)

 

የክሪስታል ፓላሱ አለቃ ፍራንክ ዲ ቦር ተመራጩ የሆነውን የ3-4-3 ፎርሜሽን ለመተው ቢሰናዱም ክለቡ ግን በሳምንትቱ መጨረሻ ላይ በሚደረገው የበርንሌዩ ጨዋታ በፊት ከስልጣናቸው ሊያሰናብታቸው ይችላሉ። ክለቡ እስካሁን በሦስት ጨዋታዎች ተሸንሾ ምንም ጎል ማስቆጠር አልቻለም። (Independent)

 

የ23, አመቱ የኤቨርተን እና የእንግሊዝ ኢንተርናሽናል ሮዝ ባርክሌይ ለቶተንሃም በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ይፈርማል። (Daily Star)

 

የሴሪአው ሻምፒዮን ክለብ ጁቬንቱሶች በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የ23 አመቱን የሊቨርፑል አማካይ ኤምሬ ቻንን ለማዛወር ይጠይቃሉ።
(Tuttosport, via Independent)

 

የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የሲቲ አጥቂ ካርሎስ ቴቬዝ እንዳለው ከሆነ ወደ ቀድሞ ክለቡ ቦካ ጁኒየርስ አርጀንቲና መመለስ በጣም ከባድ ነው ብሏል። ከቻይናው Shanghai Shenhua ጋር ያለው ውል በጣም ውስብስብ ነው ብሏልis። (Guardian)

 

የ34, አመቱ የቀድሞ አርሰናል ተከላካይ ባካሪ ሳኛ በማንቸስተር ሲቲ በነፃ ከተለቀቀ በኃላ ወደፈለገበት ክለብ መዛወር የሚችል ሲሆን ክሪስታል ፓላስ፣ ዌስትሃም እና ብራይተን ሊዛወር የሚችልባቸው ክለቦች ናቸው። (Croydon Advertiser)

 

የቶተንሃሙ የ23, አመቱ ተከላካይ አማካይ ኤሪክ ዳየር እንዳለው ከሆነ ከክለቡ ለመልቀቅ ምንም አይነት የልቀቁኝ ደብዳቤ እንደማያስገባ ተናግሮአል። የተጭዋቹ ስም ከማን.ዩናይትድ ዝውውር ጋር ተያይዞ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል። (Manchester Evening News)

 

ዋይኒ ሩኒ በቃኝ ወዳለው የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ እንደማይመለስ የተናገረ ሲሆን ይልቅ የአሰልጣኝነት ባጁን እየወሰደ በመሆኑ ወደፊት አንድ ቀን እንግሊዝን ማሰልጠን እንደሚፈልግ ተናግሮአል። (Talksport)

 

አሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ እንዳሉት ከሆነ የ25 አመቱ አማካይ ፊሊፕ ኩቲንዎን በተመለከተ ምንም እንደማይጨነቁ ተናግረዋል። ተጭዋቹ ክለቡን ለመልቀቅ ያልተሳካ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። (Guardian)

 

የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ የሆነው ኢያን ራይት እንዳለው ከሆነ የ28 አመቱ አማካይ ሜሱት ኦዚል ደጋፊዎች ወቀሳውን ትተው ድጋፍ ብቻ እንዲሰጧቸው መጠየቁን ተከትሎ ሁኔታው ‘አስቂኝ’ ነው ብሏል። (606, on BBC Radio 5 live)

 

ዌስትሃሞች በስፖርቲንግ ሊዝበኑ ዳይሬክተር ላይ ህጋዊ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ የተሰናዱ ሲሆን ግለሰቡን “liar” እና “parasite” ሲሉ ዘልፈዋቸዋል። (Daily Telegraph)

 

የቻይናዎች በአውሮፓ እግር ኳስ ላይ የሚያደርጉት የባጀት ፈሰስ ካሁን በኃላ ሊቀንስ እንደሆነ ተነግሮአል። የሃገሪቱ መንግስት ገንዘብ ከኤዢያዊቷ ሃገር ለቆ እንዳይወጣ በሚል እገዳ ለመጣል በመወሰኑ ሳቢያ እንደ አስቶን ቪላ ፣ በርኒንግሃም፣ ዌስትብሮሚች አልቢዮን እና ዎልቭስ አይነት በቻይና ባለሃብቶች የተያዙ ክለቦች ወጪ ይቀንሳሉ ተብሏል። (Birmingham Mail)

 

የቶተንሃሙ ተከላካይ ጃን ቬርቶገን ቤልጂየም ገና ሁለት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች እየቀሩአት ወደ ሩሲያው የአለም ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ ደስታውን ገልፃአል። ተከላካዩ ግሪክ ላይ ጎል ማስቆጠርም ችሏል።

 

የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ በትውልድ ከተማቸው ጣሊያን ፀሃያማ የባህር ዳርቻ ሲዝናኑ በእጃቸው ላይ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን ለማዳበር “Football English: Soccer Vocabulary for Learners of English” የሚል መፅሃፍ ይዘው ታይተዋል።
(The Sun)

 

የቶተንሃሙ ኤሪክ ዳየር እንደሚያምነው ከሆነ በእግርኳስ ላይ ለሚስተዋለው ቅጥ ያጣ ክፍያ የእግርኳስ ተጭዋቾች የምፕጨረሻዎቹ ተወቃሾች ናቸው ብሏል። (London Evening Standard)

 

ቢያንስ ሁለት የማንቸስተር ዩናይትድ ኮከብ ተጭዋሾች ሆን ተብሎ በተደበቀ ከምስል መብት በሚገኝ ገቢ ግብር ላይ በመደበቅ ክስ በHMRC ምርመራ ሊደረግባቸው ነው። (Daily Mail)

 

ለቼልሲ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት ከሆነ የ28 አመቱ አጥቂ ዲያጎ ኮስታ በቡድኑ 25 ተጭዋቾች ስኳድ ውስጥ ከተካተተ በኃላ ወደ ለንደኑ ክለብ ተመልሶ በቡድኑ ቋሚ ተሰላፊዎች መሃከል አንዱ ለመሆን ከመስራት ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የለኝም ሲል ተናግሮአል። (Telegraph)

 

ዲያጎ ኮስታ ወደ ክለቡ የማይመለስ ከሆነ ክለቡ ተጭዋቹን £50m ሂሳብ ሊያስከፍሉት አሲረዋል።
(Express)

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

እሁድ የወጡ በርካታ ዜናዎች Sunday Papers Talk

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


 
ባርሴሎናዎች በዝውውር መዝጊያው ቀን ላይ ለፊሊፕ ኩቲንዎ እና ለአንጀል ዲ ማርያ ያቀረቡት ያለቀ ሰአት የዝውውር ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሳቢያ በስፔን ሚዲያዎች ከፍተኛ ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።


 

ኬይላን ምባፔ የሪያል ማድሪድን የዝውውር ጥያቄ ባለመቀበል ወደ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ PSGዎች ካመራ በኃላ የማንቸስተር ዩናይትድን የክርስቲያኖ ሮናልዶ ዝውውር እንዳይሳካ አድርጎታል ብሏል The Sunday Times ጋዜጣ።


 

ብላንኮዎቹ በማድሪድ ደስተኛ ያልሆነውም ሮናልዶን ወደ ኦልትራፎርድ ለመመለስ ፍቃደኞች የነበሩ ሲሆን በቦታው ኬይላን ምባፔን ለማምጣት ዝግጁ ነበሩ።

ሆኖም ፈረንሳዊው ታዳጊ እና አባቱ ወደ ሪያል ማድሪድ በመዛወር የክርስቲያኖ ሮናልዶ ምትክ በመባል ትልቅ ሃላፊነትን እንዳይሸከም በመስጋታቸው እዛው ፈረንሳይ ሊቀር ችሏል።


 

ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና ኮንትራቱን አያድስም። እንደሽ Onda Cero ዘገባ ከሆነ ሜሲ በቀጣዩ ክረምት ላይ ከኮንትራቱ ነፃ ይሆናል።

የ30 አመቱ አጥቂ በአዲሱ ኮንትራቱ ዙሪያ ከክለቡ ጋር ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ፊርማውን ወረቀት ላይ አላኖረም። በኔይማር ክለቡን ለቆ ወደ PSGዎች ማምራት በክለቡ ላይ ይ8ነበረውን እምነት ቀንሶበት እሱንም አሳስቦታል።


 

በዝውውሩ መዝጊያ ቀን ላይ የሪያል ማድሪዱ አለቃ ዚነዲን ዚዳን አሌክሲስ ሳንቼዝን እንዲያዛውሩት ቀርቦላቸው የነበረ ቢሆንም ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ግን ሳይቀበለው ቀርቷል ብሏል የSpanish ህትመት Don Balon።

ቺሊያዊው ኢንተርናሽናል ከዝውውር መዝጊያው ቀን ሃሙስ በፊት ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ለመልቀቅ ከፍተኛ የሆነ ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም እና ማንቸስተር ሲቲዎች ሊያዛውሩት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ወኪሎቹ ማድሪዶች እንዲያስፈርሙት አቅርበውላቸው ነበር።

የሪያል ማድሪዱ አለቃ ዚነዲን ዚዳን ግን ብ8ክለቡ ባሉት የፊት መስመር ተሰላፊዎች ደስተኛ መሆኑን ተከትሎ ሳይቀበለው ቀርቷል።


 

የአንቶኔ ጋሬዝማን የውል ማፍረሻ አንቀፅበቀጣዩ ክረምት ላይ በአንዴ ከ€200 million ወደ €100m በግማሽ እንደሚቀንስ የስፔኑ AS ጋዜጣ ዘግቧል።

ፈረንሳዊው በቅርቡ ከአትሌቲኮ ጋር አዲስ ኮንትራት የተፈራረመ ሲሆን ምንም እንኳን በማንቸስተር ዩናይትድ እና በPSGዎች በጥብቅ ቢፈለግም እርሱ ግን ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ ለመቆየት ወስኖ ቀጥሏል።

ሆኖም የአትሌቲኮዎች የዝውውር ተሳትፎ ቅጣት በቀጣዩ ጥር የዝውውር መስኮት ላይ የሚነሳላቸው ሲሆን በጋሬዝማን ላይ ያለው ፍላጎት በድጋሚ እንደሚያገረሽ ይጠበቃል። ሆኖም ክለቡ በተጭዋቹ ጀርባ ላይ አይቀመሴ የተባለ የ€200ሚ.ዩ ዝውውር ሂሳብ ለጥፎበታል።


 

ባርሴሎናዎች የፒ.ኤስ.ጂውን አንጀል ዲ ማሪያ ለማዛወር ከፍተኛ ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም አልተሳካላቸውም ብሏል Sport ጋዜጣ።

ክለቡ ለተጭዋቹ የ€45 million ሂሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም። የካታሎኑ ክለብ ተጨማሪ ሂሳብ ለመጨመር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ሳቢያ በመጨረሻም ድርድሩ ተቊርጧል።


 

አርሰን ዌንገር ክለባቸው የሞናኮውን ቶማስ ሌማር ለማዛወር በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይም እንደሚጠይቁ አረጋገጡ።


 

Wenger ስለ ኬይላን ምባፔ: ‘ምባፔ ቀጣዩ ፔሌ ሊሆን ይችላል (the next) . የሚጔዝበት የብቃት ጫፍ ገደብ የሌለው ሊሆንም ይችላል’ (Telefoot)

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ሊቨርፑል ከ አርሰናል (የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቅድመ ምልከታ)

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

እሁድ ምሽት 12 ሰዓት በአንፊልድ

✍ እሁድ ምሽት 12 ሰዓት በደጋፊዎች ድባብ ናላን በሚያዞረው አንፊልድ ሊቨርፑል ከ አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ይፋለማሉ፡፡የአርሰናል ሙሉ ስኳድ በእለተ ሰንበት አንፊልድ ይከትማል፡፡ቀያዬቹ ሊቨርፑሎች በዘንድሮው አመት በሜዳቸው ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል፡፡ክሪስታል ፓላስን በፕሪሚየር ሊጉ እንዲሁም ሆፈንየምን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ!
★★★★★★

★★★★★★
✍ ሊቨርፑል ከ አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ በርካታ ግቦች ከሚቆጠሩባቸው ጨዋታዎች አንዱ በመሆኑ በአብዛኛው አዝናኝ ጨዋታ ይታይበታል፡፡
★★★★★★

★★★★★★
✍ በዚህ ጨዋታ በፕሪሚየር ሊጉ በየአመቱ በደርሶ መልስ በርካታ ግብ ይስተናገዳል፡፡ባለ ሜዳው ሊቨርፑል በጨዋታ ልክ እንደዚህ አመት ተከታታይ ጨዋታዋቹ ያለ ፌሊፔ ኩቲንሆ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ብራዚላዊው የጨዋታ ቀማሪ አሁንም ስሙ በስፋት ከካታሎኒያው ክለብ ባርሴሎና ጋር እየተያያዘ ነው፡፡በተጨማሪም አዳም ላላና በጉዳት አይሰለፍም፡፡በተጨማሪም ናትናኤል ክላይን በጉዳት ምክንያት የማይሰለፍ ሲሆን ምናልባት ጀርመናዊው የጌጌ ፕሬሲንግ አቀንቃኝ ከረዥም ጊዜበኃላ ማማዱ ሳኮን ሊያሰልፉ እንደሚችሉ ነው ሪፖርቶች የሚጠቁሙት፡፡
★★★★★★

★★★★★★
✍ በአርሰናል በኩል ደግሞ አርሰን ቬንገር ለመድፈኞቹ ደጋፊዎች በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስደሳች የሚባል ዜናን ነው ያበሰሩት፡፡እንደ ፈረንሳዊው ቁመተ መለሎ የመልካም እግር ኳስ አቀንቃኝ ሰው ንግግር ከሆነ ጉዳት ላይ የነበረው ሎረን ኮሼልኒ እና በተጨማሪም አሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ የአሌክሲስ በኤምሬትስ የመቆየት ነገር ግን እስካሁን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው፡፡
★★★★★★

★★★★★★
✍ ሊቨርፑል ባለፈው አመት ያደረጋቸውን ሁለቱንም የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አርሰናልን አሸንፏል፡፡ነገር ግን በተከታታይ አርሰናል 3ጊዜ (በፕሪሚየር ሊጉ ካሸነፉ) 10 አመት አልፏቸዋል፡፡አርሰናል ባለፈው አመት ከtop 6 ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች ከግማሽ በላዩን ማሳካት አልቻለም 9 ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰበው፡፡
★★★★★★

★★★★★★
✍ መድፈኞቹ Top 6 ከሚባሉት ክለቦች ጋር በተለይ ከሜዳቸው ውጪ የማሸነፍ ፎቢያ ያለባቸው ይመስላል፡፡ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ የቻሉት በJanuary 2015 ማን ሲቲን 2ለ0 በሆነ ውጤት ነበር፡፡ከዛ በኃላ ካደረጓቸው 12 ጨዋታዎች (ከTop 6 ጋር) 7 ጊዜ ሲሸነፉ 5ጊዜ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡በአንፃሩ ሊቨርፑል በ2016/17 የውድድር ዘመን ከTop 6 ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 20 ነጥብ ሰብስቧል፡፡በዚህም ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ካሉ ምርጥ 6 ክለቦች አናት ላይ ተቀምጧል (በእርስ በርስ ግንኙነት በርካታ ነጥብ በመሰብሰብ)፡፡
★★★★★★

★★★★★★
✍ በሊቨርፑል በኩል ተፅዕኖ ይፈጥራል ተብሎ ከሚጠበቁ ተጨዋቾች ዋነኛው ሳዲዮ ማኔ ነው፡፡ማኔ ባለፉት 5የሊጉ ጨዋታዎች 5ግቦች ላይ እጁ አለበት (ሶስት በማግባት ሁለት አሲስት በማድረግ)፡፡ሌላኛው ተፅዕኖ ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው ሮቤርቶ ፈርሚንሆ ነው፡፡ብራዚላዊው አማካይ ከአርሰናል ጋር ባደረጋቸው 4የሊግ ጨዋታዎች 3ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡
★★★★★★

★★★★★★
♠ እርስ በርስ ግንኙነት ♠
✔ ባለፈው አመት ሊቨርፑል ኤምሬትስ ላይ አርሰናልን 4ለ3 ያሸነፈ ሲሆን በአንፊልድ ደግሞ 3ለ1 አሸንፏል፡፡ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ውጤት እንመልከት

2017 ሊቨርፑል 3-1 አርሰናል
2016 አርሰናል 3-4 ሊቨርፑል
2016 ሊቨርፑል 3-3 አርሰናል
2015 አርሰናል 0-0 ሊቨርፑል
2015 አርሰናል 4-1 ሊቨርፑል
★★★★★★

★★★★★★
♠ ግምታዊ አሰላለፍ
☞ሊቨርፑል
ሚኞሌት
አርሎን____ሎቭረን___ማቲፕ___ሞሬኖ
ዋይናልደም____ሄንደርሰን____ቻን
ማኔ____ፈርሚንሆ____ሳላህ
★★★★

☞ አርሰናል
ቼክ
ሙስጣፋ_____ኮሼልኒ_____ሞንሪያል
ቻምበርሊን____ዣካ_____ራምሴ_____ኮላሲናች
ሳንቼዝ______ላካዜት______ኦዚል
★★★★★★

★★★★★★
☞ በርካታ የእግር ኳስ ባለሙያዎች ጨዋታው 2አቻ ይጠናቀቃል ሲሉ ገምተዋል፡፡እርሶስ ማን የሚያሸንፍ ይመስሎታል?

በጨዋታው ላይ ይምቱና ይሸለሙ!

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:

ዕረቡ ከሰአት በኃላ የወጡ በርካታ ተጭዋቾችንና ክለቦችን የተመለከቱ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎች አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ ወሬዎች

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት:


✔ ምንም እንኳን ሁለት ጊዜ የዝውውር ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ቢሆንበትም ቼልሲ አሁን €70M በማቅረብ አሌክስ ሳንድሮን ከጁቬንቱስ ማዘዋወር ይፈልጋል እንደ alciomercato ዘገባ።

ሴሪያውን በተደጋጋሚ በማንሳት በጣሊያን የነገሰችው አሮጊቷ ብራዚላዊውን የግራ መስመር ተከላካይ በክለቧ እንደምታቆይ ሙሉ እምነት አላት፡፡አሮጊቷ ልጁን በቱሪን ለማቆየትም አዲስ ኮንትራት አቅርባለታለች፡፡

 

✔ ባርሴሎና ለአራተኛ ጊዜ ከፍ በማድረግ £138M ለሊቨርፑል አቅርቧል ብራዚላዊውን ኮከብ ፌሊፔ ኩቲንሆ ወደ ካምፕ ኑ ለማምጣት እንደ Sky Sports ዘገባ።

የsky sports ዘገባ እንደሚያስረዳው ካታሎኒያኑ በአንፊልድ ያልተረጋጋውን ኮከብ በቅድሚያ £101M በመክፈል ቀሪውን £37M ደግሞ ቀስ በቀስ በቦነስ መልክ ነው መክፈል የሚሹት፡፡

 

✔ ቼልሲ ለአሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን £35M አቅርቧል እንግሊዛዊው አማካይ ከአርሰናል መውጣት እንደሚፈልግ መናገሩን ተከትሎ እንደ The Sun ዘገባ።

የ24 አመቱ መድፈኛ በኤምሬትስ የሚቀረው የ1 አመት ብቻ ኮንትራት ሲሆን በለንደን ሌላኛውን የሊጉን ሻምፒዮን ቼልሲ መቀላቀል ይፈልጋል፡፡

 

✔ ማን ዩናይትድ አሁን ያለውን ስብስብ የበለጠ ለማጠናከር የቫሌንሲያውን የመሀል ተከላካይ ኤስኩዌል ጋራይ የማዘዋወር ፍላጎት አላቸው እንደ The Sun ዘገባ።

ቀያይ ሰይጣኖቹ የ30 አመቱን ተከላካይ ብቃት ለመመልከት ጥቂት ሰዎችንም ወደ ስፔን ልከዋል፡፡ጋራይ በቶተንሀም፣ጁቬንቱስ እና ቤኔፊካም ጭምር ይፈለጋል፡፡

 

✔ ለወራት ጉዳት ላይ የነበረው አርጀንቲናዊው ተከላካይ ማርኮስ ሮሆ ትናንት ከቡድን አጋሮቹ ጋር ልምምድ መስራት ጀምሯል፡፡ [MU]

 

✔ ብሌስ ማቱዲ ስለ ጁቬንቱስ ፦ “በጣም ደስ የሚሉ የቡድን ጓደኞች ናቸው እዚህ ያሉት በሚገርም አኳኋን ነው የተቀበሉኝ” ሲል ስለ አዲሱ ክለቡ ጁቬንቱስ ተናግሯል፡፡ [Juve]

 

✔ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የዚነዲን ዚዳንን ስልክ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ጋቦናዊው አጥቂ ሪያል ማድሪድን የመቀላቀል ጉጉቱ ከፍተኛ ነው፡፡ (Source: Don Balon)

 

✔ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በማንቸስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አመት የመቆየት ከፍተኛ ጉጉት ስላለው ባሳለፍነው አመት ከሚከፈለው ከፍተኛ ደሞዝ ዝቅ ሊያደርግ ነው፡፡ (Source: Daily Star)

 

✔ [የተረጋገጠ] ሳውዝሀምተን ዌስሊ ሆይዴስን ከላዚዮ ማዘዋወሩን ይፋ አድርጓል፡፡ቅዱሳኖች ለተጨዋቹ £15.4M የከፈሉ ሲሆን በሴንት ሜሪ እንዲቆይም የ5 አመት ኮንትራት አስፈርመውታል፡፡

 

✔ በሳምንቱ መጨረሻ በስቶክ ሲቲ የተሸነፉት መድፈኞቹ ከደጋፊዎቻቸው በጥቁቱም ቢሆን ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ የሞናኮውን ቶማስ ሌማር የማስፈረም ፍላጎታቸው በድጋሚ ተቀስቅሷል ፡፡ (Source: Le10Sport)

 

✔ የባርሴሎናው አጥቂ ሙኒር ኤልሃዳዲ የክሪስታል ፓላስ ራዳር ውስጥ ገብቷል ፡፡ (Source: Mundo
Deportivo)

 

✔ ባርሴሎና የቀድሞው ተጨዋቹን ኔይማር ኮንትራቱን አላከበረም በሚል ምክንያት £7.8M ይገባኛል በማለት ከሷል ፡፡ (Source: Sky Sports)

 

✔ ቶተንሀም ጉዳት ላይ ለሚገኘው እንግሊዛዊ የኤቨርተን አማካይ ሮዝ ባርክሌ £20M አቅርቧል፡፡ቶተንሀም ከከተማ ተቀናቃኙ ቼልሲ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡ (Source: Telegraph)

 

✔ [የተረጋገጠ] ኢንተር ሚላን ጃሆ ካንሴሮን ከቫሌንሲያ በውሰት አስፈርሟል፡፡በውሉ ላይ ኢንተር ልጁ እስከ 2018 በሚያሳየው አቋም ደስተኛ ከሆነ በቋሚነት ማስፈረም እንደሚችል የሚገልፅ አንቀፅም አለ፡፡ (Source: Inter_en)

 

✔ ቦሩሲያ ዶርትመንዶች በኦስማን ዴምቤሌ ጉዳር ለመደራደር ከዚህ በኃላ ፍላጎቱ የላቸውም ፡፡ (Source: SkySports)

 

✔ ከፊዮረንቲና ከቀናት በፊት ታላቁ ኤሲ ሚላንን የተቀላቀለው ኒኮላ ካሊኒክ በሚላን 7 ቁጥር መለያን እንደሚለብስ ተረጋግጧል ፡፡ (Source: acmilan)

 

✔ ሮማ አልጄሪያዊውን የሌስተር ሲቲ ኮከብ ሪያድ ማህሬዝ ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት ውድቅ ቢደረግበትም አሁን ሂሳቡን ወደ £50M ከፍ በማድረግ በድጋሚ ጥያቄውን አቅርቧል ፡፡ (Source: Sun Sport)

 

✔ ለረዥም አመታት በአሮጊቷ የቆየው ክላውዲዮ ማርኪሲዮ ከጁቬንቱስ መልቀቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል ፡፡ (Source: Sun Sport)

በመረጡት ማህበራዊ መንገድ ለጔደኛዎ ያጋሩት: